About Me

My photo
Independence, Neutrality, Rule of the Law, Impartiality and Transparency.

Wednesday, December 14, 2011

THE 2010 POST ELECTION EVALUATION AND ITS SIGNIFICANCE


It is beyond doubt that democratic election in a given country shall meet certain criteria. A democratic election shall live up to the international process and principles of democratic election. Speaking of basic international processes and principles presupposes the existence of a constitution. The standard requires the existence of constitutionally recognized independent election commission and specifies the frequency of election and requirement of the political parties to play the game by the rules of the country. It is also stated as one of the international standards that post election evaluation should be conducted shortly after the independent election commission or board announced the winner party.
It is known that Ethiopia has hosted fair, free, peaceful, democratic and legitimate general election in 2010. Meanwhile, it is important to conduct a post election evaluation in order to identify strengths and weaknesses and this is the reason why the board conducted the first post election evaluation.
The evaluation was conducted under the patronage of the National Electoral Board of Ethiopia and it aimed at identifying the weak and strong sides of the fourth general election and rectifying the weakness and capitalizing on the strength for holding free, fair, peaceful, democratic and legitimate elections in the future.
Questionnaire needed for this evaluation were prepared in collaboration with the central statistics authority in a scientific and easily understandable and answerable manner. 
The main points included in the questionnaire are the structure, accessibility and security of election centers and election offices ,the process of voters’ and candidates’ registration, civics and voters awareness ,the right to elect and the participation of women in election; competence and impartiality of election officers; working relationship and exchange of information between the board and stakeholders; election campaign, complaint handling procedure, election law, voting process, vote counting and announcement of results, etc…
The data were collected during the post 2010 election evaluation from 77 zones of the nine regions and two city administrations using the statistical sampling method. 18,881 persons including voters, election officers, public observers, justice organs at different level, administrative organs, mass media, civic societies and political parties from the sampled 154 constituencies and 916 polling stations responded to the questionnaire.
This questionnaire completed by the stakeholders has been collected from all regions of the country compiled by statisticians using the Statistical Package for the Social Sciences (SPSS). After the compilation of the evaluation result, the board presented the draft to stakeholders and included their feedback.
The significance of the post election evaluation is to enable the board understand the desire of the voters and improve its election procedures so as to increase their participation and boost the role of political parties. It will also enable the attainment of international principles of election for developing the democratization process of the country.
As a result, the compiled evaluation result created the capacity to identify the weaknesses and strengths observed in the 2010 national election, to identify loopholes in the election law and its implementation for indicating legal and procedural modifications and formulate the next strategy on the basis of the evaluation.
One of the values advocated by the board is to follow the trend of consultation with all stakeholders and accept appropriate feedbacks as inputs to capitalize on the strength and rectify the openings. The Board held consultations with political parties on issued regulations and directives, financial subsidy and airtime allocated to parties and election time schedule, etc… this is an indication that the board has forged a solid relationship with stakeholders.
The 2010 post election evaluation enables the Board secretariat to recognize its strength, weakness, opportunities and challenges whereby, resuming the strength and rectifying weakness, using opportunities exhaustively and reducing possible challenges. As a result, it will have a huge contribution in ensuring the freeness, fairness, peacefulness, democratic and legitimacy of future elections.   
It is a known fact that Ethiopia registered all round growth in the past consecutive years. The government has formulated the five years Growth and Transformation Plan to capitalize on these gains. In this regard, the 2010 post election evaluation result will have huge contribution in solidifying its responsibilities laid down in the plan.

FIVE YEARS PLAN TO REALIZE THE BOARD’S VISION

Vision refers to the aspiration of a nation, institution and an organization for a future success. The vision of our country is to see that Ethiopia becomes a nation where, through popular participation and the consent of its peoples, democracy and good governance reign, social justice prevail, and where being emancipated from poverty, the country enjoys a middle income status.

Despite their similar nature, there is some difference between vision and mission. Mission focuses on routine activities and improvable issues. Vision on the other hand, shows our aspiration to the future thereby encouraging and inspiring us to towards that end.

Like any other governmental offices, the National Electoral Board of Ethiopia has its own vision and mission.

Vision:-
“To see the realization of strong constitutional system wherein the Nations, Nationalities and Peoples of Ethiopia exercise their right of electing and being elected in a peaceful and fair manner.”

Mission:-
“To develop the understanding of the society on civics to let them understand their right to elect and be elected for contributing their role in the continuation of the democratization process; conduct fair, free and  impartial election throughout the country with the equal participation of all nations, nationalities and peoples of the country.”

The Board has designed different strategies to realize this mission. One of it is the five years strategic plan which is formulated on the basis of the five Years Growth and Transformation Plan of the country.

The main purpose of the strategic plan to be implemented in 2010/11 – 2014/15 is to harmonize the Board’s practices with the five Years Growth and Transformation Plan of the government, to satisfy the growing demand of stakeholders, to raise the satisfaction rate of the public and put in place international standard electoral system.

This five Years strategic plan has been prepared after assessing the overall functions of the Board and its current status and enables the Board to play a constructive role in the democratization process of the country in the next five years and have the capacity to efficiently discharge its functions. The Growth and Transformation Plan indicates that good governance and democratization is one of the areas worth special attention for speeding up the implementation of the plan and put the country among the list of middle income earning countries by 2015.

The current level of development in the country is the result of democratization and good governance system building undertaken in the past years. Extensive and coordinated effort needs to be exerted for the realization of the Growth and Transformation Plan and ensure the continuation of the development process. Election is the pillar of a democratic system and the only means for citizens to ensure their constitutional right of being administered by their elected administrators. To ensure this right of the public, it is important to ensure the reliability and legitimacy of the election process by the stakeholders and particularly, the voters. Hence, the National Electoral Board of Ethiopia is doing all necessary steps to play its part in the areas of good governance, democratization and public participation.

In addition to the Growth and Transformation Plan, there are other considerations for developing the strategic plan of the Board. These are: the 2009/10 budget year performance report and 2010/11 budget year’s plan, the 2010 Post election evaluation conducted by the Board, discussions held with stakeholders and feedbacks as well as discussions with employees of the office.

On the basis of these considerations, the Board developed a strategic plan containing six key strategic issues needed for the effectiveness of the institution and the country as well. These strategic issues are:

The Board five year strategic plans and its focal routes are:-
1. To enable the existence of strong skilled man power, monitoring and following up of property and finance.
2. To strengthen the performance of employees and motivation.
3. To strengthen the information documentation, application and flow trend.
4. To enable the voters have ample knowledge about the board.
5. To have electoral constituency delimitation considering the current size of population.
6. To raise the number of women in manipulating election and in being candidates.

The inclusion of these key strategic issues and other activities within the five years strategic plan of the Board helps it achieve better performance in the next five years. It also accelerates and paves the way for the vision of the Board.

Tuesday, December 13, 2011

የመድበለ ፓርቲ ሥርዓቱን ለማጠናከር የተወሰደ እርምጃ


ሀገራችን ኢትዮጵያ ከ1983 ዓ.ም ድረስ በተማከለ የፖለቲካ ስርዓት ትተዳደር ሥለነበር ዜጎች የፈለጉትን አስተሳሰብ ይዘው የፖለቲካ ድርጅት በማቋቋም የሚንቀሳቀሱበት ህጋዊ ስርዓት የተፈቀደ አልነበረም፡፡ ይህ ዓይነቱ ስርዓት ባለመፈጠሩ ሀገሪቱ ለብዙ ዓመታት የዘለቀ የእርስ በርስ ጦርነት ስታስተናግድ ቆይታለች፡፡ እንደዚህ ዓይነቱ ችግር የሚፈታው የሐሳብ ልዩነትን የሚያስተናግድ የመድበለ ፓርቲ ስዓርት ሲኖር ብቻ ነው፡፡ የመድበለ ፓርቲ ስርዓት በሀገራችን  የተጀመረው ግንቦት 2ዐ ቀን 1983 ዓ.ም. ወዲህ በደርግ ውድቀት ማግስት ነው፡፡ የደርግ መንግሥት መገርስን ተከትሎ በተፈጠረው የዲሞክራሲ ፍንጭ በመጠቀም በሀገር ውስጥ እና በውጭ ያሉ የነፃነት እንቅስቃሴ የሚያካሂዱ የፖለቲካ ድርጅቶች ተሰባስበው የሽግግር መንግሥት በመመስረት እንደ ህገ መንግስት የሚያገለግል የሽግግር ቻርተር አፀደቁ ፡፡ የሽግግር ቻርተሩን ተመስርቶ በሀገሪቷ የተለያየ አስተሳሰብ ያላቸው የፖለቲካ ድርጅቶች አማራጫቸውን ለህዝቡ አቅርበው መወዳደር የሚችሉበትን የተደላደለ ሜዳ የሚፈጥርና የምርጫ እንቅስቃሴን በገለልተኝነት የሚመራ ተቋም ማቋቋም አስፈላጊ በመሆኑ የምርጫ ኮሚሽን በአዋጅ ቁጥር 11/1984 ተቋቋመ፡፡ የምርጫ ኮሚሽን ተልዕኮውን ጨርሶ በአዋጅ ሲፈርስ በምትኩ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የምርጫን ስራ በገለልተኝነት የማስፈፀም ተልዕኮ ተሰጥቶት ተተካ፡፡
አሁን በሥራ ላይ ያለው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በተሻሻለው የምርጫ ህግ ቁጥር 532/1999 ዓ.ም. ተቋቁሞ፣ ሁሉንም የፖለቲካ ፓርቲዎች በገለልተኝነት፣ በእኩልነትና በታማኝነት እያገለገለ የምርጫ እንቅስቃሴዎችን በብቃት እየመራ ይገኛል፡፡ የሀገራችንን መድበለ ፓርቲ ስርዓት እንድጎለብት እና የውድድር ሜዳው የተመቻቸ እንዲሆን ቦርዱ ባወጣቸው ከ 16 በላይ ለምርጫ አፈጻጸም የሚረዱ ደንቦችና መመሪያዎች ፖለቲካ ፓርቲዎችን እና ሌሎች ከባለድርሻ አካላት በማማከርና ጠቃሚ አስተያቶቻቸውን በማካተት በስራ ላይ እንድውሉ በመደረጉ የምርጫ አፈጻጸማችን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ እንዲመጣ አግዟል፡፡ በተጨማሪም ከባለድርሻ አካላት ጋር በመመካከር አቅማቸው እንድጎለብት የስልጠና፣ አውደ ጥናትና የውይይት መድረኮችን በማመቻቸት በርካታ የአቅም ግንባታ ስራዎችን ሰርቷል፡፡
በመሆኑም ሀገራችን ኢትዮጵያ የመድብለ ፓርቲ ሥርዓት ማካሄድ ከጀመረች ሁለት አሥርት ዓመታትን አሳልፋለች፡፡ በነዚህ ዓመታቶች ሥርዓቱ ተጠናክሮ እንዲቀጥል፣ ዜጐች በፈለጉት የፖለቲካ አስተሳሰብ ተደራጅተው መንቀሳቀስ እንዲችሉ ተደርጓል፡፡ በሽግግር መንግስት ወቅት እና ከ1987 ዓ.ም እስከ 2003 ዓ.ም. በተካሄዱ የጠቅላላ፣ የአካባቢ፣ የማሟያ ምርጫዎች እና የህዝበ ውሳኔዎች  የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች በየጊዜው ተሳትፎአቸው እያደገ የመጣበት ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡
መንግስት በፓርላማ መቀመጫ ካላቸው ፓርቲዎች ጋር በሚወጡ ህጎች እና አዋጆች ላይ ቀድሞ እየተወያየ በህዝብ ተዎካዮች ምክር ቤት ጸድቀው እንድወጡ እያደረገ ይገኛል፡፡ በተጨማሪ ለፖለቲካ ፓርቲዎች የፋይናንስ ድጋፍ በማድረግ ቁርጠኝነቱን አሳይቷል፡፡ ቦርዱ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር እየተመካከረና እየተወያየ እንደሚሰራ ሁሉ፣ በ 2003 በጀት ዓመትም ይህንኑ አጠናክሮ በማስቀጠል፤ በማሟያ ምርጫ፣ በ2002 ድህረ ምርጫ ዳሰሳ ጥናት ላይ ውይይትና ምክክር እንዲሁም በምርጫ ህጉ፣ በፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ አዋጅ፣ በመንግስት የፋይናንስ ድጋፍ አጠቃቀም እና በሁለንተናዊ አመራር ላይ ስልጠና በመስጠት አቅማቸው እንድጎለብት አድርጓል፡፡ ይህ የመንግስትና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያልተቋረረት ይበልጥ የፖለቲካ ምህዳሩ እንዲሰፋና ሁሉም ህጋዊና ሰላማዊ ፖለቲካ ፓርቲዎች በእኩልነት እና በፍትሃዊነት እንድንቀሳቀሱ ለማስቻል ነው፡፡
የአገራችን መድብለ ፓርቲ ሥርዓት ተጠናክሮ፣ ዴሞክራሲ ሥርዓቱ ይበልጥ እንዲጐለብት እና  የፖለቲካ ፓርቲዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ የፋይናንስ አቅም እንዲኖራቸው ያስፈልጋል፡፡ የፋይናንስ አቅም ሲኖራቸው አባሎቻቸውንና ደጋፊዎቸውን ለማንቀሳቀስ እድል ይሠጣቸዋል፡፡ ለፖለቲካ ፓርቲዎች ዋናው የፋይናንስ ምንጭ ሆኖ የሚያገለግለው ከአባሎቻቸውና ከደጋፊዎቻቸው የሚሠበሰቡት ገንዘብ ቢሆንም ከዚህ በተጨማሪም  የአገሪቱ የኢኮኖሚ አቅም በፈቀደው መልኩ ቦርዱ ከመንግሥት በጀት በማስፈቀድ የገንዘብ ድጐማ ይሠጣቸዋል፡፡ ከመንግሥት የሚሠጠው የገንዘብ ድጐማ በፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ አዋጅ ቁጥር 573/2000 ዓ.ም አንቀጽ 42 ንዑስ አንቀጽ 1 እና አንቀጽ 45 ንዑስ አንቀጽ 1 መሠረት ለፖለቲካ ፓርቲዎች የሚሠጠው ድጋፍ በፌዴራል ወይም በክልል ምክር ቤቶች ባላቸው መቀመጫ ብዛት መሠረት እንደሆነ ተደንግጓል፡፡ ከመንግሥት ለፖለቲካ ፓርቲዎች የሚሠጠው ድጋፍ በምርጫ ወቅትና ከምርጫ ውጭ በየዓመቱ ለዕለት ከዕለት ተግባራት ማከናወኛ የሚውል ነው፡፡ በመደበኛነት በየዓመቱ የሚጠው የገንዘብ ድጐማ በምርጫ ወቅት እንደማይሠጥ እና የራሱ የምርጫ ድጐማ ብቻ እንደሚሠጥ በአዋጁ ተደንግጓል፡፡
በዚህ መሠረት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አዋጁ ከወጣ በኋላ በ2002 ዓ.ም. ለምርጫ ሥራ የሚውል ከመንግሥት የተመደበን ገንዘብ ለ63 ተወዳዳሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች በተቀመጠ የክፍፍል ቀመር መሠረት እንዲከፋፈሉ አድርጓል፡፡ በበጀት ዓመቱም ለመደበኛ የዕለት ተዕለት ተግባራትን የሚያከናውኑበት 10 ሚሊዮን ብር ከመንግሥት በጀት አስፈቅዶ እንደተለመደው ፖለቲካ ፓርቲዎች በክልልና በፓርላማ ባላቸው መቀመጫ ብዛት ህጉን ተከትሎ አከፋፍሎ እየተጠቀሙ ይገኛሉ፡፡ መንግሥት በሠጠው የገንዘብ ድጐማ ተጠቃሚ የሆኑት 8 የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫ ያላቸው እና 9 የክልል ም/ቤቶች መቀመጫ ያላቸው ፖለቲካ ፓርቲዎች ናቸው፡፡
ቦርዱ ከመንግሥት አስፈቅዶ ለፖለቲካ ፓርቲዎች የሠጠው የድጐማ ገንዘብ የመድብለ ፓርቲ ሥርዓቱን ለማጠናከር እና የአገራችን ዴሞክራሲ የላቀ ደረጃ እንዲደርስ ታሳቢ ያደርገ ነው፡፡ በመሆኑም ገንዘቡን የወሰዱ የፖለቲካ ፓርቲዎች የፓርቲያቸውን የዕለት ተዕለት ተግባር፣ የህዝቡን የፖለቲካ ግንዛቤ በማዳበር፣ ዜጐች የሀገሪቱ ፖለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ ንቁ ተሳትፎ እንዲኖራቸው ማድረግ፣ የፓርቲያቸውን ዓላማ ማስረፅን፣ በህዝቡና በመንግሥት ተቋማት መካከል መልካም ግንኙነት እንዲፈጠር የማድረግ ተግባራትን እንዲያከናውኑበት የተሰጠ ድጋፍ ለተባለለት ዓላማ አውለው መገኘት የሚኖርባቸው ሲሆን ቦርዱም በወቅቱ ተጠቅመው እንዲያወራርዱ የመከታተል ኃላፊነቱን ይወጣል፡፡
ጠቅላላ የገንዘቡ ድጋፍ ለጠቅላላ መቀመጫ ብዛት ተካፍሎ የተገኘው ገንዘብ መጠን የአንድ ወንበር ዋጋ ይሆናል፡፡ በዚሁ መሠረት ፖለቲካ ፓርቲዎች ባገኙት መቀመጫ መጠን ተሠልቶ ተከፋፍሏል፡፡ በአጠቃላይ ይህ የፋይናንስ ድጋፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተጨማሪ አቅም አግኝተው እንዲንቀሳቀሱ የውድድር መድረክ የሚከፍት ነው፡፡ ከመንግሥት ለፖለቲካ ፓርቲዎች የሚጠው የገንዘብ ድጋፍ የአገሪቱ የኢኮኖሚ አቅም በፈቀደ መልኩ ቀጣይነት ያለው በመሆኑ ወደፊትም ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡






የሥነ - ዜጋዊ እውቀትና ክህሎት ለዴሞክራሲያዊ ምርጫ!


የዴሞክራሲ ፅንሰ - ሃሳብ አንድን ማህበረሰብ በጋራ ተጠቃሚ የሚያደርግ ወይም ለማህበረሰቡ ጉዳት ሊያስከትል በሚችል ጉዳይ ላይ የማህበረሰቡ አባላት በሚያደርጉት የጋራ ውይይት ችግሩን የሚፈቱበት እና እያንዳንዱ ተወያይ እኩል ተደማጭነት የሚያገኝበት ሆኖ በሚቀርቡ የመፍትሔ ሃሳቦች ላይ ጥቂቶቹ የአብዛኛውን አማራጭ ሃሳብ በማክበር ወደ ተግባር የሚለወጥበት ሥርዓት ነው፡፡ ሂደቱ ጥቂቶች የሚደመጡበት፣ የብዙሃን ድምፅ የሚከበርበት እና የአባላት ድምፅ እኩል የሆነበት ነው፡፡
ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት የሚገለጽበት ዋንኛ መንገድ ምርጫ ነው፡፡ ምርጫ ለህዝብ የቆመ እና የዜጐች ሰብዓዊ እና ዴሞክራሲያዊ መብቶች የሚከበርበት መንግሥታዊ ሥርዓት እንዲኖር ከሚያደርጉ የሉዓላዊነት መገለጫዎች አንዱ እና ዋነኛው ነው፡፡ ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ የመንግሥታዊ ሥልጣን ምንጭ ህዝቡ መሆኑና የመንግሥት ተጠያቂነትም ለህዝብ መሆኑ ነው፡፡ ስለሆነም ህዝቡ ይህን ታላቅ ሀገራዊ ኃላፊነቱን መወጣት እንዲችል ሥነ - ዜጋዊ እውቀት እና ክህሎት ማዳበር ይጠበቅበታል፡፡

አሁን በስራ ላይ ያለው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰኔ 19 ቀን 1999 ዓ.ም ኃላፊነቱን ሲረከብ ጽ/ቤቱ ያለበትን ችግር በጥናት ለይቶ እና የመፍትሄ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ነበር ወደ ስራ የገባው፡፡ በችግርነት ከተለዩትና መፍትሄ ከሚያስፈልጋቸው መካከል የመራጮችና የስነ-ዜጋ ትምህርት አሰጣጥ ሁኔታ አንዱ እና ዋነኛው ነበር፡፡ ቦርዱ ለችግሩ መፍትሄ ለመስጠትም  ከሁለት አመት በላይ ጊዜ ወስዶ የመራጮችና የስነ-ዜጋ ትምህርት ማስተማሪያ ማኑዋል ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን በጥንቃቄ አዘጋጅቷል፡፡ ይህ ማስተማሪያ ማኑዋል በቦርዱ ፀድቆ ተግባራዊ እንዲሆን ተወስኗል፡፡
ቦርዱ የተጣለበትን ምርጫ የማስፈፀም ታላቅ ሃገራዊ አደራ ለመወጣት ባለፉት 4 ዙሮች ባካሄዳቸው የጠቅላላ እና የአካባቢ ምርጫዎች ህዝቡ በእውቀት ላይ የተመሠረተ ምርጫ ማከናወን እንዲችል ልዩ ልዩ ስልቶችን በመጠቀም በመላ ሀገሪቱ የመራጮችና የሥነ - ዜጋ ትምህርት በመሥጠት የህዝቡን ሥነ - ዜጋዊ እውቀትና ክህሎት ለማዳበር እና ለማሳደግ ባደረገው ጥረት፣ ህዝቡ በተለያዩ ዙሮች በተሳተፈባቸው ምርጫዎች በየጊዜው እየዳበረ የመጣ በእውቀት ላይ የተመሠረተ ምርጫ በማካሄድ አመርቂ ውጤት ለማየት የቻለበት ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡

ይህን የህዝቡ ሥነ - ዜጋዊ እውቀት እና ክህሎት በላቀ ደረጃ ማሳደግ እንዲቻል ቦርዱ በመላ ሀገሪቱ ጥቅም ላይ የሚውልወጥነት ያለው ይዘትና ስልትን አጠቃሎ የያዘ የመራጮችና የሥነ - ዜጋ ትምህርት ማስተማሪያ ማኑዋል አዘጋጅቷል፡፡ ይህ ማስተማሪያ ማኑዋል 2002 .. በተደረገው ምርጫ ለማስተማሪያነት ጥቅም ላይ ውሎ ከፍተኛ ውጤት አስገኝቷል፡፡ በዚህ ዓመትም ይበልጥ በባለድርሻ አካላት ተገቢው ምክክር እና ውይይት ተደርጐበት ዳብሮ በማኑዋልነት በቦርዱ ፀድቋል፡፡
የማስተማሪያ ማኑዋሉ በሀገራችን ባሉ የክልሎች የሥራ እና የትምህርት ቋንቋዎች በመተርጐም ላይ ነው፡፡ ሁሉም ዜጐች ሥነ ዜጋዊ እውቀት እና ክህሎትን ማሳደግ እንዲችሉ እና ምክንያታዊ ሆነው የሚበጃውንና የሚጠቅማቸውን ለመምረጥ የሚያስችላቸው ግንዛቤ የሚያገኙበት ይሆናል፡፡

ቦርዱ ይህን ትምህርት ለመላው የሀገራችን ህዝብ እንዲዳረስ ለማድረግ ልዩ ልዩ ስልቶችን ቀይሶ ወደ ተግባር ገብቷል፡፡ በዚህ ረገድ የሚጠቀሰውና ወደ ሥራ የተገባበት የብሔራዊ እና ክልላዊ የመገናኛ ብዙሃንን ሬዲዮ በመጠቀም በልዩ ልዩ ቋንቋዎች ትምህርቱ ለህዝቡ እንዲደርስ ማድረግ ነው፡፡ ከዚህ አንጻር ቦርዱ ከአማራ ክልል መገናኛ ብዙሃን፣ ከኦሮሚያ ክልል መገናኛ ብዙሃን፣  ከሶማሌ ክልል መገናኛ ብዙሃን፣ ከአዲስ አበባ መገናኛ ብዙሃን፣ ከደቡብ ክልል መገናኛ ብዙሃን እንዲሁም ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እና ከትግራይ ድምፅ ወያኔ ሬዲዮ ጋር ማኑዋሉን ለማስተማር የሚያስችል ለአንድ ዓመት የውል ስምምነት ለመፈጸም ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡
ለአንድ ዓመት በሣምንት ለሁለት ተከታታይ ቀናት ለሁለት ሰዓት በሬዲዮ የሚተላለፈው ትምህርት ለመገናኛ ብዙሃኑ በውሉ መሠረት ወጥነት ባለው መልኩ ትምህርቱ ሳቢ እና ማራኪ በሆነ መንገድ መሥጠት እንዲችሉ ቦርዱ ውል ለተዋዋሉት የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ሥልጠና ለመሥጠት ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡  ከዚህ ሥልጠና በኋላም በሁሉም ክልሎች የመራጮችና የሥነ - ዜጋ ትምህርት በቋሚነት ይሠጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
የሥነ - ዜጋ ትምህርት ዜጐች ስለ መንግሥት፣ ስለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት፣ ስለህዝብ የሥልጣን ባለቤትነት፣ ስለ ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶቻቸው፣ ስለማህበራዊና ህገ - መንግሥታዊ መብትና ግዴታዎቻቸው፣ ስለ አካባቢ ልማት፣ ስለተፈጥሮ ሀብት፣ ስለ ድህነት ቅነሳወዘተ ግንዛቤና እውቀት የሚያዳብሩበት ትምህርት ነው፡፡
ይህ ትምህርት ዜጐች በእውቀት ላይ የተመሠረተ ምርጫ እንዲያከናውኑ የሚረዳቸው ሲሆን ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት ለማስመዝገብ፣ መልካም አስተዳደርን ለማስፈንና ብልሹ አሠራሮችን ለማስወገድ እንዲሁም የሚፈጠርባቸውን ወቅታዊ ችግሮችን በሠለጠነ መንገድ እንዲፈቱ የሚያደርግ እና ዘለቄታዊ ልማት የሚያስገኝ ነው፡፡
ከዚህ አንጻር እያንዳንዱ ዜጋ ሥነ - ዜጋዊ ባህሪያቱ የጐለበተ መሆን ይኖርበታል፡፡ ለዚህም  የመራጮችና የሥነ - ዜጋ ትምህርት የላቀ ሚና በመጫወት ዜጐችን ለማህበራዊ እድገት እንዲነሳሱ፣ ማህበራዊ ተሳትፎአቸውንም በማሳደግ መብትና ግዴታውን በማክበር እና በማስከበር የግልፅነትና የመቻቻል እሴቶችን በማጐልበት ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓቱ መዳበር የሚያበረክተው አስተዋፅኦ ጉልህ ነው፡፡
ይህን ለመወጣትም ሥነ - ዜጋዊ እውቀት ያስፈልጋል፡፡ በዚህ ረገድ ሁሉም ዜጐች የሀገራቸውን የፖለቲካ ሁኔታ፣ በህግ የተሰጡትን መብቶችና ግዴታዎች፣ የማህበረሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ትስስሮች፣ የዜግነት ድርሻቸውን፣ ማህበራዊ ችግሮችንና መፍትሔዎቻቸውን እንዲሁም በህግ የተሠጡትን መብቶችና ግዴታዎችን ጠንቅቀው በማወቅ ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ የበኩላቸውን አስተዋፅኦ ማበርከት ይጠበቅባቸዋል፡፡
ቦርዱ ይህን በመገንዘብ መላው የሀገራችን ህዝቦች ሥነ - ዜጋዊ እውቀት እና ክህሎት አዳብረው በሀገራቸው ዴሞክራሲያዊ ግንባታ ሂደት በንቃት እንዲሳተፉ የሚያደርጋቸው የሥነ ዜጋና የመራጮች ትምህርት በስፋት ለመሥጠት በመንቀሳቀስ ላይ መሆኑ የጉዳዩ አስፈላጊነት ምን ያህል ከፍተኛ እንደሆነ ያመላክታል፡፡ 
የመራጮች ትምህርት በዋንኛነት ለመራጩ ህዝብ የሚሠጥ ሲሆን ይህም መራጩ ህዝብ ሊያውቀው የሚገባውን መረጃ  በቅድሚያ አውቆ በምርጫ እንዲሳተፍ የሚያስችለው ትምህርት ነው፡፡ ትምህርቱ በተለይ እድሜያቸው 18 ዓመት እና ከዚያ በላይ ለሆናቸው ዜጐች እና በምርጫ ለመሳተፍ ብቁ ለሆኑ ዜጐች ስለምርጫ ምንነት፣ ስለምርጫ ጥቅም፣ ስለምርጫ አካሄድና ሥርዓት፣ ስለምርጫ ሂደት ደረጃዎች፣ ስለመራጮች አመዘጋገብ፣ ስለድምፅ አሠጣጥ፣ወዘተ የሚማሩበት ነው፡፡
የመራጮች ትምህርት በምርጫ ወቅት በስፋት ቢስጥም እስከ ሚቀጥለው የምርጫ ወቅት ድረስ ህዝቡ ሥነ - ዜጋዊ እውቀቱ እና ክህሎቱን የሚያዳብሩ ተከታታይነት ያላቸው ግንዛቤ ማሳደጊያዎችን በስፋት መሥጠት እጅግ ተመራጭ ነው፡፡ ለዚህም ነው ቦርዱ ከዚህ መሠረታዊ ፅንሰ - ሀሳብ ተነስቶ ለመላው የሀገራችን ህዝቦች የሥነ ዜጋዊ እውቀት እና ክህሎት ማሳደጊያ ትምህርት ለመሥጠት የተነሳሳው፡፡ ስለሆነም የመራጮችና የሥነ - ዜጋ ትምህርት በሀገራችን መሥጠቱ ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ትልቅ አስተዋፅኦ ያለውና መራጩ ህዝብ በነጻነት ያለማንም ጣልቃ ገብነት፣ ያለፍርሃት፣ ያለተፅዕኖ እና ከማንኛውም መደለያ ነጻ በሆነ መልኩ ድምፅ በመሥጠት በእውቀት ላይ የተመሠረተ ውሳኔ ለመሥጠት የሚያስችለው ትምህርት ነው፡፡